በማንኛውም የDCPS ትምህርት ቤት ውስጥ አዲስ ለሆኑ ተማሪዎች፣ ተማሪዎን ለማስመዝገብ ዕድሜን የሚያረጋግጥ ሰነድ ያስፈልጋል። እባክዎን ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ይመልከቱ:
የዕድሜ ማረጋገጫ አማራጮች
ከእነዚህ 1 (አንድ) ሰነድን ያቅርቡ:
1. የልደት የምስክር ወረቀት
2. የሆስፒታል መዝገቦች
3. የቀድሞ ትምህርት ቤት መዝገቦች
4. ፓስፖርት (Passport)
5. የጥምቀት የምስክር ወረቀት
በየዓመቱ ሁሉም ተማሪዎች የዲስትሪክቱ ነዋሪነታቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ ያስፈልጋቸዋል። የትምህርት ቤት ኃላፊዎች የውስጠ˗ድርጅታዊ ማጋራት ሂደትን በመከተል ነዋሪነታቸውን ማረጋገጥ፣ የOTR ማመልከቻ መሙላት፣ ወይም የነዋሪነት ማረጋገጫን ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት አማራጮች ማቅረብን ጨምሮ፣ ቤተሰቦች ይህን መስፈርት ለማሟላት በርካታ አማራጮች አሏቸው። ስለነዋሪነት በተመለከተ ጥያቄዎች ካለዎት፣ የትምህርት ቤትዎን የምዝገባ ኃላፊ ያነጋግሩ።
እባክዎን ያስተውሉ:
1. የአስመዝጋቢው ግለሰብ ስም፣ እንደነዋሪ ማረጋገጫነት የቀረበው መረጃ ላይ በሙሉ ካለው ስም ጋር አንድ ዓይነት መሆን አለበት።
2. የአስመዝጋቢው ግለሰብ አድራሻ፣ እንደነዋሪ ማረጋገጫነት የቀረበው መረጃ ላይ በሙሉ ካለው አድራሻ ጋር አንድ ዓይነት መሆን አለበት።
የነዋሪነት ማረጋገጫ አማራጮች
ከእነዚህ 1 (አንድ) ሰነድ ያቅርቡ:
1. ክፍያ የተደረገበት ቁራጭ (Pay Stub)
2. የዲሲ መንግሥት የገንዘብ እርዳታ
3. የተረጋገጠ (Certified) የዲሲ ታክስ ቅጽ-D40
4. የውትድራ የመኖሪያ ትዕዛዛት
5. የኤምባሲ ደብዳቤ
ወይም
ከእነዚህ 2 (ሁለት) ሰነዶችን ያቅርቡ:
1. የዲሲ ሞተር ተሽከርካሪ የምዝገባ ወረቀት
2. የዲሲ የመንጃ ፈቃድ/መንጃ ፈቃድ ያልሆነ መታወቂያ (ID)
3. የሊዝ ስምምነት፣ ክፍያ ከተደረገበት ደረሰኝ ጋር
4. የዩቲሊቲ (Utility) ማስከፈያ ወረቀት፣ ክፍያ ከተደረገበት ደረሰኝ ጋር
እያንዳንዱ አባሪ (attachment) ከ50MB መጠን ማለፍ የለበትም።